January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አርባ ምንጭ ከተማ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ተመለሰ

አርባ ምንጭ ከተማ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተመልሷል።

በ23ኛ ሳምንት ምድብ “ለ” ተጠባቂ ጨዋታ አርባ ምንጭ ከተማ ቦዲቲ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም አርባ ምንጭ ከተማ ሶስት ጨዋታዎች እየቀሩት ከአንድ የውድድር ዘመን በኃላ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለሱን አረጋግጧል፡፡

አርባ ምንጭ ከተማ በ2015 የውድድር ዘመን ከፕሪሚየር ሊጉ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ የሚታወስ ሲሆን÷ በዓመቱ ወደ ሊጉ መመለስ መቻሉንም የክለቡ መረጃ ያመላክታል፡፡