መርከቧ ፉጂያን የሚል ስያሜ የተሰጣት ሲሆን በሻንጋይ ስራ ጀምራለች
ቻይና መርከቧን ለመስራት ስድስት ዓመት የፈጀባት ሲሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ በሙከራ ላይ ነበረች ተብሏል
ቻይና 60 አውሮፕላኖችን የሚይዝ የጦር መርከብን ስራ አስጀመረች፡፡
የዓለማችን ሁለተኛዋ ልዕለ ሀያል ሀገር ቻይና የባህር ሀይሏን የሚያዘምን ዘመናዊ የጦር መርከብ ይፋ አድርጋለች፡፡
ፉጂያን የሚል ስያሜ የተሰጣት ይህች የጦር መርከብ በአንድ ጊዜ 60 አውሮፕላኖችን የመያዝ አቅም እንዳለውም ተገልጿል፡፡
80 ሺህ ቶን ክብደት ያላት ይህች መርከብ ላለፉት ስድስት ዓመታት በግንባታ ላይ የቆየች ሲሆን ከፈረንጆቹ 2022 ጀምሮ ደግሞ የባህር ላይ ሙከራ ስታደርግ እንደቆየች ሽንዋ ዘግቧል፡፡
ቻይና 66 ሺህ እና 60 ሺህ ቶን የመጫን አቅም ያላቸው ሻንዶንግ እና ሊያውኒንግ የተሰኙ ሁለት የጦር መርከቦች ያላት ሲሆን ሶስተኛውን እና ዘመናዊው ጦር መርከብ ባለቤት ሆናለች፡፡
አዲሷ ፉጂያን የጦር መርከብ ኤሌክትሮ ማግኔቲክ ሲስተም የተገጠመላት ሲሆን ከፍተኛ እና ክብደት ያላቸውን ጦር አውሮፕላኖች እንዲነሱ እና እንዲያርፉ ማድረግ ያስችላልም ተብሏል፡፡
የጦር መርከቧ በደቡባዊ ቻይና ባህር በኩል በአሜሪካ፣ ፊሊፒንስ እና ቬትናም በኩል ሊነሱ ለሚችሉ ተጽዕኖዎች እና ሌሎች ጥቃቶችን ለመከታተል እና ምላሽ ለመስጠት እንደሚያስችላት በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
Al-ain
More Stories
ዶናልድ ትራምፕ 47ኛ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ
የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ
የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)