January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኤች አይ ቪ ኤድስን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ሀገሪቱ በ2030  የያዘችዉን ግብ ለማሳካት ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ ቀረበ፣

የኤች አይ ቪ ኤድስን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ሀገሪቱ በ2030  የያዘችዉን ግብ ለማሳካት ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ ቀረበ፣

በሸካ ዞን የኤች አይ ቪ ህክምና አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት እና በዞኑ ጤና መምርያ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት የ9 ወራት አፈፃፀም  ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የሸካ ዞን ጤና መምሪያ የኤችአይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት አቶ ጥላሁን ካመቶ የኤች አይ ቪ ኤድስን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ሀገሪቱ በ2030 ለማሳካት የያዘችውን ግብ  ለማሰካት ባለድርሻ አካላት በትኩረት  ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

የህዝብ ቁጥር በሚበዛባቸዉ የልማት ፕሮጀክቶች አካባቢ የሚታየዉን የHIV AIDS ስርጭት ከመከላከል አንፃር ቀሪ ስራዎች እንዳሉ አቶ ጥላሁን አንስተዋል፡፡

በመድረኩ የዞኑ ሁሉም መዋቅሮች የ9 ወራት አፈፃፀማቸውን አቅርበው ውይይት የተደረገበት ሲሆን ዉስንነት የታዩባቸዉ ተግባራት በቀጣይ እንዲሻሻሉ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ኤች አይ ቪ ኤድስን  በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ መንግስት የበጀት አቅም ዉስንነት ያለበት በመሆኑ በዘርፉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ የዉይቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል ፡፡

በአፈፃፀም ግምገማው የዞን ጤና መምርያ የዳይሬክቶሬቱ አስተባባሪ እና ባለሙያዎች፣  የሆስፒታል ሜድካል ዳይሬክተር  እና ሌሎች የሚመለከታቸው  ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

ዘጋቢ :- ልጃለም ማሞ