በጣሊያናዊው የካርሎ አንቼሎቲ አሰልጣኝነት ዘመን ክርስቲያኖ ሮናልዶ በርካታ ጎሎችን በማስቆጠር ቀዳሚው ነው
አንቼሎቲ ዳግም ወደ ሪያል ማድሪድ ከተመለሱ በኋላም ስኬታማነታቸው ቀጥሏል
ጣሊያናዊው አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲ በ2014 ነበር ከዜነዲን ዚዳን ሪያል ማድሪድን የተረከበው።
የስፔኑን ክለብ በተረከቡበት አመት ለ10ኛው የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ክብር ያበቁት አንቼሎቲ፥ በርካታ ኮከብ ጎል አስቆጣሪዎችን በማፍራትም ይታወቃሉ።
ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በካርሎ አንቸሎቴ አሰልጣኝነት የሪያል ማድሪድ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ነው፤ ሮናልዶ 66 ጎሎችን አስቆጥሯል።
ፈረንሳዊው አጥቂ ካሪም ቤንዜማ ሮናልዶን ይከተላል፤ በ45 ጎል።
ጋዜዝ ቤል፣ ሰርጂዮ ራሞስ እና ጀምስ ሮድሪገዝ እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
በ2021 ዳግም ዳግም ወደ ሪያል ማድሪድ የተመለሱት አንቼሎቲ፥ በ2022 የሻምፒዮስን ሊግ ዋንጫን ማንሳታቸው ይታወሳል።
ጣሊያናዊ አሰልጣኝ በኤሲ ሚላን በ2003 እና 2007 የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ማንሳታቸው ይታወሳል።
More Stories
ኢትዮጵያና ዑጋንዳ ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ
በፕሪሚየር ሊጉ ሊግ ማንቸስተር ዩናይትድ እና አስቶንቪላ አቻ ተለያዩ
ማንቼስተር ሲቲ እና ኒውካስል ዩናይትድ ነጥብ ተጋሩ