July 2, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 29ኛ መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ዉሳኔዎችን አሳለፈ

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 29ኛ መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ዉሳኔዎችን አሳለፈ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደዉ 29ኛ መደበኛ ስብሰባ በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተዉ የክልሉ የኢንቨስትመንት ዕንቅስቃሴ አስመልክቶ የቀረበዉን ሪፖርት ነዉ።

ምክር ቤቱ ባደረገዉ ግምገማ ክልሉ ከተመሰረተ ወዲህ በርካታ የኢንቨስትመንት ዕንቅስቃሴዎች መኖሩን በጠንካራ ጎን ገምግሟል።ከለዉጥ በኃላ ብዙ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች መመላሳቸዉን ምክር ቤቱ ተመልክቷል።መሬት ወስደዉ ወደ ስራ ያልገቡት ላይ የተጀመረ ዕርምጃ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አባላቱ ጠይቀዋል።የክልሉን ዕምቅ አቅም ያገናዘበ የኢንቨስትመንት ክላስተር ፍኖተ ካርታ እንዲዘጋጅም አቅጣጫ አስቀምጧል።ወደ ስራ የገቡ ኢንቨስትመንቶች የፈጠሩት የስራ ዕድልም ከፍ ባለ ቁጥር እንዲጨምር እንዲሁም የሚያከናወኑት ኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነት ላይ ትኩረት እንዲደረግ መስተዳድር ምክር ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ምክር ቤቱ በሁለተኛ አጀንዳነት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮ ጵያ ህዝቦች ክልልና በጋምቤላ ክልል መካከል የተፈረመን የሁለትዮሽ የሠላምና ልማት ትብብር ስምምነት ላይም ተወያይቷል።በዉይይቱም የትብብር ስምምነቱ መፈረምና የፎረም መቄቋም ወሰኝ እርምጃ መሆኑን አመልክተዉ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ተከፍቶ በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገባ አቅጣጫ በማስቀመጥ ትብብር ፎረሙ ወደስራ እንዲገባ ምክር ቤቱ ዕዉቅና ሰጥቷል።

መስተዳድር ምክር ቤቱ በሶስተኛነት የተመለከተዉ የአስፈጻሚ አካላትን እንደገና ለማሻሻል፣ለማደራጀትና ስልጣንና ተግባራት ለመወሰን የወጣ ረቂቅ አዋጅን ነዉ። አሁን ያለዉ መንግስታዊ አወቃቀር ለአዳጊ ተለዋጭ ሁኔታዎች ወቅታዊ ምላሽ ለመስጠት ፣ የተልዕኮ ትስስርና እርስበርስ ተናቦና ተቀናጅቶ የመስራት ፋይዳ ታሳቢ አድርጎ እንደገና በመቃኘትና በመከለስ አንጻራዊ ማስተካከያ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀዉን ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ በማጽደቅ ወደ ምክር ቤቱ መርቶታል።

በአራተኛ ደረጃ የተለያዩ ተቋማትን ስልጣንና ተግባር ለመዘርዘር የወጣ ደንብ ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ አሳልፏል።

በዚህም መሰረት

1.የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ ረቂቅ ደንብ፣

2.የመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደርና ኤጄንሲን ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ ደንብ፣

3.የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስልጣንና ተግባር ለወወሰን የወጣ ረቂቅ ደንቦች ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

ምክር ቤቱ በአምስተኛ አጀንዳነት የተመለከተዉ ክልሉ የራሱ ሚዲያ እንዲኖረዉ ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀዉን

‘የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ” ለማቋቋም የወጣዉን ረቂቅ አዋጅ ነዉ።

የክልሉ መስተዳድር ምክርቤት ክልላዊ የሚዲያ ኔትወርክ መመስረት ረቂቅ አዋጅ ሲሆን አሁን በደረስንበት የቴክኖሎጂ ዘመን ትክክለኛና ጥራቱን የጠበቀ መረጃ ከሚዲያ ተወዳዳሪነትና ከመረጃ ተደራሽነት አኳያ ለክልሉ ያለው አበርክቶ የላቀ መሆኑ ተገንዝቧል።

የሚዲያው መቋቋም የመንግስትን ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ ዕሳቤዎች፣ ተልዕኮና ተግባራት በቅርበትና በፍጥነት ወደ ህዝቡ እንዲደርሱ በማድረግ የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች እንዲሳለጡ የሚያስችል እንደሆነም ተገልጿል።

በሌላ በኩልም ሚዲያው ለኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እድገት ብሎም ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ከሚኖረው ሚና ባሻገር ለህብረብሄራዊ አንድነት መጎልበትና የወንድማማችነት እሴት ሥር እንዲሰድ በማገዝ በመረጃ የበለጸገ ማህበረሰብ እንዲፈጠርና በክልሉ ሁለንተናዊ ብልጽግና እንዲረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑም ታምኖበታል።

ክልላዊ የሚዲያ ኔትወርክ ማቋቋም የክልሉ ህዝብ የእርስ በርስ ትስስር እንዲፈጠርና አንዱ ከሌላው በጎ ባህልና ልምድ እንዲለዋወጥ ምቹ መደላደልና መድረክ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑ ስለሚታመን፤

የሚዲያ ኔትወርክ ተቋቁሞ ስራ ላይ እንዲዉል የቀረበዉን የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ወደ ክልሉ ምክር ቤት ሂዶ እንዲጸድቅ ወስኗል።

# የክልሉ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን