በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲካሄድ የቆየው 21ኛው የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶችና 17ኛው የባህል ፌስቲቫል ውድድር በዛሬው ዕለት ፍፃሜውን አግኝቷል
“የባህል ስፖርቶች ልማት ለሀገር ገጽታ ግንባታ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት ከሚያዚያ 12 እስከ 20/2016 ዓ.ም ድረስ ሲካሄድ በቆየው 21ኛው የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶችና 17ኛው የባህል ፌስቲቫል ውድድር ላይ ተጠናቋል።
በውድድሩና ፌስቲቫሉ ሲሳተፍ የቆየው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የባህል ስፖርቶችና የባህል ፌስቲቫል ውድድር ልዑክ በከፍተኛ ፉክክር በፈረስ ሸርጥ በወንዶች እና በሻህ ውድድር በሴቶች ክልሉ ሁለት ወርቅ ሜዳልያዎች እንዲሁም በባህል ፌስቲቫል ትርዕይት 2ኛ ደረጃ በመያዝ 1 ብር በአጠቃላይ ክልሉ 4 ዋንጫዎችን መሰብሰብ ችሏል።
በዚሁ ውድድር በፈረስ ሸርጥ በወንዶች ወጣት አሸብር አለማየሁ እና በሻህ ውድድር በሴቶች ወጣት ነፃነት ተመስገን ለክልሉ ሁለት ወርቅ ሜዳልያዎችና ዋንጫዎችን አስገኝቷሉ።
በውድድሩ ማጠናቀቂያ ላይ በባህል ስፖርቶች ውድድር እና ፌስቲቫል ላይ ለተሳተፉ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች አስተናገጁ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የዋንጫና የሰርተትኬት ሽልማት አበረከቷል። ዝግጅቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ ላበረከቱት አስተዋፅኦም አመስግነዋል ሲል የክልሉን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮን ጠቅሶ የዘገበዉ የክልሉ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ነዉ።
More Stories
በኤፍ ኤ ካፕ 4ኛ ዙር ድልድል ሩበን አሞሪም ከሩድ ቫን ኔስትሮይ አገናኝቷል
የዱባይ ማራቶን በኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ፍጹም የበላይነት ተጠናቀቀ
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሠራተኞች መካከል የነበረው አለመግባባት በውይይት መፈታቱ ተገለጸ