በምርጥ ዘር አመራረትና አያያዝ ላይ ለባለድርሻ አካላት ሲሰጥ የነበረ ስልጠና ተጠናቀቀ።
የክልሉ ምርጥ ዘር ድርጅት ከክልሉ ግብርና ቢሮ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) ጋር በመተባበር ለምርጥ ዘር አባዥ አውቶግሮወርስና ለባለደርሻ አካላት በአመያ ከተማ በዘር ብዜት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተጠናቋል።
አርሶ አደሩ ምርጥ ዘርን በማባዛት ተቋሙንና ክልሉን ማገዝ እንደሚገባ የገለጹት የክልሉ የመንግሥት ረዳት ተጠሪ አቶ ነጋ አበራ ጥራት ያለዉን ምርጥ ዘር በማሳቸው በመዝራት ምርታማነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
በምርጥ ዘር አመራረትና ጥራት ቁጥጥር ሂደት ላይ በቀረበው ሰነድ ላይ ወይይት የተደረገ ሲሆን በኮንታ ዞን ኮይሻ ወረዳ ቡላ ሀማኮ ቀበሌ በድርጅቱ የእርሻ ማሳ የስራ ጉብኝት ተካሂዷል ።
በጉብኝቱም ወቅት ገለጻ የሰጡት የተቋሙ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ እምሩ ወዬሳ ተቋሙ ዘርን በተመጣጣኝ ዋጋ ለአርሶ አደሮችና ለአልሚ ባለሀብቶች በማቅረብና በአከባቢው ለአደጋ ስጋት ጊዜ ምላሽ ለመስጠት ለምግብነት የሚሆኑ ሰብሎችን በስፋት ለማልማት መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በጉብኝቱ ወቅት ለተሳታፊዎች በዘርፉ ባለሙያዎች በቦታው እየተሰራ ስላለው የበልግ ሰብል ተጨማሪ ማብራሪያ ተሰጥቷል ።
በማሳ ጉብኝት የተሳተፉ የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የዘር ብዜት ሥራ መጀመሩ የአከባቢውንና የአጠቃላይ የክልሉን አርሶ አደሮች የዘር ችግር በቅርበት ለመፍታት ዕድል እንደሆነ በማንሳት ተቋሙ የዘር ብዜት ስራ በራሱ ማሳ መጀመሩና የዘርፉ ባለሙያዎች በበሽታና ተባይ ቁጥጥር ስራና ለአርሶ አደሩን ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ትኩረት መስጠታቸውን እንደ ጠንካራ ጎን በማንሳት ፤
የብዜት ጣቢያና አርሶአደሩ ቅንጅት ማጠናከር እንዳለበት፣ የዘር ብዜት በሁሉም ዞን ላይ ተደራሽነት እንዲሆን፣ አልሚ ባለሀብቶች የአከባቢው አርሶአደሮች ድርጅቱ ግኑኝነት በቀጣይ እንዲጠናከር አሳስበዋል ።
የዘር ብዜት ተግባር ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በሁሉም ዞኖች መሬትን በመረከብ ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጅት ላይ መሆኑን የገለጹት የተቋሙ ሀላፊ አቶ ኢምሩ የአካባቢውን ዘር ብዜት በምርጥ ዘር ለመተካትና እጥረቱን ለመቅረፍ ከኦሮሚያ ምርጥ ዘር ድርጅት ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነ አንስተዋል ።
በስልጠናውና የመስክ ጉብኝቱ የክልሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የዞን መምሪያ ኃላፊዎች፣ አልሚ ባለሀብቶች፣ አርሶ አደሮች እንዲሁም ሌሎች ባለደርሻ አካላት ተሳትፈዋል ሲል የዘገበው የክልሉ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው።
More Stories
የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ
የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እለት በርካታ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈችፒዮንግያንግ በጥቂቱ ሰባት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሷን የጃፓን የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል