
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በክረምት የስልጠና መርሃ ግብር የሚሳተፉ ተማሪዎችን ምዝገባ ጀመረ
ኢንስቲትዩቱ የስልጠና መርሐግብሩንም ይፋ አድርጓል።
በሶስተኛ ዙር የክረምት ስልጠና መርሃ ግብር የሚሳተፉት የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆኑ እና ስልጠናውን በሳምንት ለ4 ቀናት መከታተል የሚችሉ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ገልጿል።
በመጪው ክረምት ለተከታታይ ሁለት ወራት ለሚሰጠው ስልጠናም ፍላጎት ያላቸው ታዳጊዎች ከዛሬ ሚያዝያ 17 እስከ ግንቦት 07/2016 ባሉት ተከታታይ ቀናት መመዝገብ እንደሚችሉ አስታውቋል።
ስልጠናው ከሀምሌ 1 እስከ ጳጉሜ 1/2016 ዓ.ም ለሁለት ወራት የሚቆይ ሲሆን በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዙሪያ የንድፈሀሳብና የተግባር ትምህርት ለሰልጣኝ ተማሪዎች ይሰጣል ተብሏል።
ስልጠናው ከሚያተኩርባቸው መካከል የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሰረታውያን፣ ሮቦቲክስ፣ ፕሮግራሚንግ፣ ማሽን ለርኒንግ እና ሌሎችም ይገኙበታል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸናን ጨምሮ የኢንስቲትዩቱ የስራ ኃላፊዎች፣ አሰልጣኞችና ተማሪዎች መርሐግብሩ ይፋ ሲደረግ ተገኝተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።