July 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኮሙኒኬሽን ዐቅምን ማጎልበት ለመረጃ ተደራሽነትና ለሀገራዊ መግባባት መሰረት መሆኑ ተገለጸ ::

የኮሙኒኬሽን የኮሙኒኬሽን ዐቅምን ማጎልበት ለመረጃ ተደራሽነትና ለሀገራዊ መግባባት መሰረት መሆኑ ተገለጸ:: የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከፌዴራል መንግሥት ተቋማትና ከክልሎች ለተውጣጡ የኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት አመራሮች ለአንድ ሳምንት ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ተጠናቅቋል። “ሀገራዊ መግባባትና የኮሙኒኬሽን ተቋማት ሚና” በሚል ጭብጥ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞች፣ የሠላም ባህል ግንባታ፣ ሀገራዊ የልማት ፖሊሲ አቅጣጫዎችና የወል ትርክት ግንባታ ላይ አተኩሮ የተሰጠው ሥልጠና፣ የኮሙኒኬሽን ዘርፉን ዐቅም የሚያጎለብት መሆኑ ተመላክቷል።በሥልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የሥራ አቅጣጫ ያስቀመጡት የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ፥ “ሥልጠናው የዘርፉን ዐቅም በመገንባት የመረጃ ተደራሽነትን ለማረጋገጥና ሀገራዊ መግባባትን ለማጠናከር እየተደረጉ ካሉ ጥረቶች አንዱ ነው” ብለዋል።ሥልጠናው በፌዴራል መንግሥት መስሪያ ቤቶችና በክልሎች ደረጃ እስከታችኛው መዋቅር እና ባለሙያ ድረስ መውረድ እንዳለበትም አሳስበዋል።የሕዝብን የመረጃ ፍላጎት ለማሟላት የኮሙኒኬሽኑ ሚና ጉልህ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፤ ሁሉንም የሚዲያ አማራጮች በመጠቀም ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችን፣ ዕቅዶችንና አፈጻጸሞችን ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን ከአገልግሎት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።