July 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢትዮጵያን የጋራ ሀብት የሆነዉ ታላቁ የህዳሴ ግድብ በቀሩት ግዜያት ሰርቶ ለማጠናቀቅ የጋራ ርብርብ ያስፈልጋል ዶ/ር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጋሾ::

የኢትዮጵያን የጋራ ሀብት የሆነዉ ታላቁ የህዳሴ ግድብ በቀሩት ግዜያት ሰርቶ ለማጠናቀቅ የጋራ ርብርብ ያስፈልጋል ዶ/ር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጋሾ

ክልል አቀፍ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተኳህዷል።

በንቅናቄ መድረኩ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጅነር ነጋሽ ዋገሾ የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ኩራት የሆነ አጠቃላይ የኢኮኖሚ አቅማችንን ልቀይር የምችል ና በድፕሎማስያዊ ዘርፍም ትልቅ ድል ያስመዘግብንበት የጋራ ሀብታችን ነዉ ብለዋል።

የግድቡ ግንባታ አፈፃፀም ከአጠቃላይ ስራዉ 95 በመቶ መጠናቀቁ የተጠቆመ ስሆን ይህም የኢትዮጵያዊያን የጋራ ርብርብ ውጤት ነው ብለዋል።

ይህ ርብርብ በሎሎች ዘርፎች መደገም እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያን የጋራ ሀብት የሆነዉ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

ግድቡ ስራ ከተጀመረበት መጋቢት 2003 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በተለያዩ የማህበራዊ መሰረቶች የህብረተሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑንም አንስተዋል።

የህዝብ ተሳትፎ በተመለከተ አጠቃላይ እንደ ሀገር 19 ቢሊዬን ብር በእስከአሁኑ የተሰበሰበ ስሆን እየተገባደደ ባለው አመትም በሀገር አቀፍ ደረጃ 300 ሚሊዬን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱ ተጠቁሟል።

የክልሉ ህዝብም እንደወትሮው ተሳትፎውን እንድያጠናክር ምክትል ርዕሰመስተዳድሩ ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ ጠይቀዋል።

የክልሉ የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈትቤት ኃላፍው አቶ አክልሉ ወልደሚኪኤል የቀጣይ ተግባራት ንቅናቄ ሰነድ ያቀረቡ ስሆን በ2016 አመተ ምህረት ቀጣይ ሶስት ወራት ዉስጥ 96 ሚሊዬን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ጠቁመዋል።

ለስራው መሳካት አመራሩ ህዝቡን በማስተባበር እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።

የንቅናቄ መድረኩ ተሳታፍዎችም ህብረተሰቡ ለህዳሴ ግድብ በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ ስያደርግ መቆየቱን ጠቁመው አሁንም ድጋፉን ከማስተባበር ጀምሮ የድርሻቸውን እንደምወጡ ገልፀዋል።

በቸርነት አባተ