January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የክልሉ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው።

የክልሉ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው።የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት የአስፈጻሚ ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ክንውን በቦንጋ ከተማ እየተገመገመ ይገኛል፡፡የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ባስተላለፉት መልዕክት መድረኩ በበጀት ዓመቱ በዘጠኝ ወራት በመደበኛ እና በካፒታል ፕሮጀክቶች የተከናወኑ ስራዎች አፈጻጸም በመገምገም እንዲሁም የተቋማቶችና የፌዴራል የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት በክልሉ ባደረጉት ምልከታና ድጋፍ መነሻ የተሰጡ ግብረ መልስ ላይ በጋራ በመወያየት የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ማስቀመጥ ላይ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።በዚህም በሰላም፣ልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ለህዝቡ በገባነው ቃል መሠረት ምላሽ ለመስጠት የተቀናጀ ጥረትና ትጋት ያስፈልጋል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።በመድረኩ በዘጠኝ ወራቶች የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል በክፍተት የታዩትን በማረም ለቀጣይ ቀሪ ወራቶች የ90 ቀናት ዕቅድ በማዘጋጀት መረባረብ እንደሚያስፈልግ ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ጠቅሰዋል፡፡እስከ ነገ ድረስ በሚቆየው የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ሁሉም አስፈፃሚ ተቋማት የዘጠኝ ወራት የተግባር አፈጻጸም መገምገምና የዘጠና ዕቅድ ላይ ዉይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።በመድረኩ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ጸጋዬ ማሞ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉና የሴክተር መስሪያ ቤቶች ኃላፊዎች እና ሌሎች አስፈፃሚ አካላት እየተሳተፉ ናቸው ሲል የዘገበው የክልሉ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው።