July 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የREDD+ ፕሮጀክት በምዕራፍ አንድ ፕሮግራሙ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ እንዲሁም በኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም የተሻለ ስራ መስራቱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን አከባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለዉጥ ቁጥጥር ቢሮ አስታወቀ ።

የREDD+ ፕሮጀክት በምዕራፍ አንድ ፕሮግራሙ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ እንዲሁም በኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም የተሻለ ስራ መስራቱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን አከባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለዉጥ ቁጥጥር ቢሮ አስታወቀ ።

የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ኢንጂነር አስራት ገብረ ማርያም እንደገለፁት ክልሉ በተፈጥሮ ሀብት የታደለ በመሆኑ ይህንን የተፈጥሮ ፀጋ መሰረት በማድረግ ፕሮጀክቶች የተፈጥሮ ሀብቱን በማልማትና በመጠበቅ የተፈጥሮ ሀብት አካል በሆነዉ ደን ላይ ኑሮአቸውን መሰረት ያደረጉት የማህበረሰብ ክፍሎችን የመደገፍል ሥራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል ብለዋል።

ከነዚህም ፕሮጀክቶች ዉስጥ በክልሉ 29 ወረዳዎች የሚንቀሳቀሰው የREDD+ ፕሮግራም ከ2010 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በመጀመርያ ምዕራፍ ቆይታዉ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቶ አሁን ላይ የ2ኛ ምዕራፍ ስራ ለመስራት ወደ ተግባር መግባቱን ገልፀዋል።

የREDD+ ፕሮጀክት ባለፉት ዓመታት በመተግበሩ ለተለያዩ ነገሮች ተላልፎ አደጋ ሊደርስበት የሚችለው የተፈጥሮ ደን ህልውናው ተጠብቆ እንዲቆይ ከማድረግ አንፃር ሰፊ ስራ መስራቱን የጠቆሙት ኃላፊው ለአብነትም ከ2መቶ 81 ሺ ሄክታር በላይ ደን ተከልሎ በ2 መቶ14 አሳታፊ የደን አስተዳደር ማህበራት እንዲጠበቅ ማድረጉን ገልፀዋል።

በዚህም 33ሺ ዘጠኝ መቶ በላይ አባላት በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ መሆናቸዉን በመጠቆም።

ፕሮጀክቱ ደንን ከመጠበቅ አልፎ ሽፋኑ እንዲያድግ ሰፊ አበርክቶ ነበረዉ ያሉት ዶክተር አስራት 13 ሺህ ሄክታር አዲስ ተከላ በማድረግ ክልላዊ የደን ሽፋንኑን 42 በመቶ ማድረስ መቻሉን ገልፀዋል።

በሌላ በኩልም ፕሮጀክቱ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ በተጨማሪ በኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራሙ ባለፉት 5 ዓመታት 3መቶ 11 ሚሊዬን ብር በላይ ገንዘብ ለክልልና ዞን ማስተባበርያ ዩኒት እንዲሁም ለ29 ወረዳዎች አገለግሎት መስጠት መቻሉን ገልፀዉ በዚህም መንግስት ተደራሽ ማድረግ ያልቻለበት አከባቢ ላይ የሀብት ዉስንነት ክፍተት በመሙላት በኩል ድርሻዉ የጓላ ነዉ ብለዋል።

በአሳታፍ ደን ማህበራት የተደራጁ የማህበረተሰቡ ክፍሎች በዶሮ እርባታ ፣በግ በማሞከት ፣ከብት ማደለብ ፣ በንብ ማነብና መሰል ስራዎች መሰማራታቸውን አስረድተዋል።

እንደ ዶ/ር አስራት ገለፃ ከሆነ ፕሮጀክቱ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም በተጨማሪ በዘላቂነት ሀብት ሆኖ ልቀጥል የሚችል ከቡና ገለባ የድንጋይ ከሰል የሚያመርቱ ማሽኖች ወደ ክልሉ የገቡ ስሆን በቅርቡ ሼድ ስራ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ በፊት የቡና ገለባ ሲቃጠል አካባቢ ላይ እያሳደረ የነበረዉ ተፅዕኖ የሚቀንስና ከሰል ለማምረት ሲባል ደን ላይ የሚደርሰዉን ጫና ለመቀነስ ከመርዳቱ በላይ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች እንድሁም የተገለሉ የማህበረተሰብ ክፍሎችን በማደራጀት የስራ ዕድል ከመፍጠር አንፃር ፕሮጀክቱ ዘርፍ ብዙ ስራዎችን እየሰራ መቆየቱን ተናግረው በምዕራፍ ሁለት ፕሮግራም ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ ስራዎች ተጠናክረዉ ይቀጥላሉም ብለዋል።

ዘጋቢ :- ቸርነት አባተ