




የሸካ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የአስፈጻሚ መምሪያዎች የ2016 በጀት ዓመት የ 9ወራት የተግባር አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አጠቃላይ አመራር በተገኙበት በቴፒ ከተማ ማካሄድ ጀመረ።
የ9 ወራት ተግባር ግምገማ መድረኩን የመሩት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ እንደተናገሩት በዚህ አፈጻጸም ላይ ጉለት በታዩት አካባቢ ትኩረት በማድረግ ቶሎ ፈጥኖ በመውጣት የጋራ ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
በቀር ሦስት ወራት ውስጥ የ90 ቀናት ዕቅድ በማቀድ ሁሉም የጋራ ቅንጅትና ርብርብ በማድረግ ለስኬታማነቱ ቅንጅታዊ ስራ እንደሚጠይቅ ዋና አስተዳዳሪው በመድረኩ አሳስበዋል።
በመድረኩ ባለፉት 9 ወራት የተከናወኑ ተግባራት በጥልቀት በመገምገም ጉለቶችንና ጥንካሬዎችን በመለየት ለቀር ወራት የጋራ ርብርብ ለማድረግ የስራ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል።
በዚሁ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በኢኮኖሚ ፣በማህበራዊ እና በአስተዳደራዊ ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት ቀርበው በጥልቀት ውይይት እንደሚደረግባቸው ለማወቅ ተችሏል ሲል የዞኑ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ዘግቧል።
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ