ለ50 ሺህ መምህራንና የትምህርት አመራር የብቃት ስልጠና ሊሰጥ ነው
በመጪው ክረምት ለ50 ሺህ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የብቃት ስልጠና እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል ።
ስልጠናው የትምህርት ጥራት ችግርን ለመቅረፍና የመምህራን ብቃትን ለማሳደግ ያለመ ሲሆን÷ በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ይሰጣል ነው የተባለው።
በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን እና የትምህርት አመራር መሪ ስራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ(ዶ/ር) መምህራኑ የሚሰለጥኑት በሚያስተምሩት ትምህርትና በማስተማሪያ ዘዴዎች መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል ።
ለ42 ሺህ መምህራን 120 ሰዓት፤ ለ8 ሺህ የትምህርት አመራሮች ደግሞ የ60 ሰዓት ስልጠና እንደሚሰጣቸው የተገለፀ ሲሆን ÷ሲያጠናቅቁም ፈተና እንደሚወስዱ ነው ስራ አስፈጻሚው የተናገሩት፡፡
ስልጠናው በመምህራንና የትምህርት አመራሩ ላይ ያለውን የማስተማር ዘዴዎችና የእውቀት ክፍተት ለመሙላት እንደሚያግዝ ታምኖበታል፡፡
More Stories
የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ
የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እለት በርካታ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈችፒዮንግያንግ በጥቂቱ ሰባት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሷን የጃፓን የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል