November 21, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የግል የትምህርት ተቋማት መንግሥት እንደ ሀገር የጀመራቸውን የጥራት ማስጠበቂያ ስልቶች ለማሳካት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲያበረክቱ ተጠየቀ።

ባሁኑ ወቅት በትምህርት ዘርፍ እንደ ሀገር ለተመዘገበው የውጤት ማሽቆልቆል ዋነኛ ምክንያት ተደርጎ የሚወሰደው በትምህርት ጥራት ላይ ወቅቱን የዋጀ እርምጃ አለመወሰዱ መሆኑን ብዙሃኑ የሚስማሙበት ነው።

ከዚህ ውድቀት በፍጥነት ማገገም ይቻል ዘንድም መንግሥት በዘርፉ የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የፖሊሲ ክለሳ በማድረግ በየደረጃው ወሳኝ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል።

የግል የትምህርት ተቋማት ለዚህ ውጥን መሳካት ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ትውልድን በሥነ ምግባር በማነጽ ጥራት ያለውን ትምህርት በመስጠቱ ረገድ ተቋማቸው ጠንክሮ እየሠራ መሆኑን በቴፒ ከተማ የአዘነ ውቤ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር የሆኑት አህመድ የሱፍ ተናግረዋል።

እንደማሳያም ትምህርት ቤታቸው ባለፈው ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከክልሉ ግንባር ቀደም ውጤት ማስመዝገቡን በመግለጽ።

ትምህርት ቤቱ እያከናወነ ለሚገኘው ጠንካራ ተግባር ማበረታቻ ይሆን ዘንድም የሸካ ዞን አስተዳደር በቴፒ ከተማ ለማስፋፊያ ግንባታ የሚሆን መሬት መስጠቱን ገልጸዋል።

የቴፒ አልፋልህ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር የሆኑት አቶ አብዲ የሱፍ ትምህርት ቤታቸው መንግሥት ያስቀመጣቸውን የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ተግባራትን በተገቢው እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ትውልድን በሥነ ምግባር በማነጽ ብቁ ሀገር ተረካቢ ዜጋን ለማፍራት እየተሠራ ስለመሆኑም ተናግረዋል።

በቴፒ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የፈተና አስተዳደር ባለሙያ አቶ ታረቀኝ ተስፋዬ በበኩላቸው በትምህርት ዘርፍ አስፈላጊውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲቻል የግል የትምህርት ተቋማት ሚና የጎላ መሆኑን ተናግረው ተቋማቱ መንግስት በዘርፉ የጣለባቸውን ሀላፊነት በተገቢው እንዲወጡ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

ለዚህም ጽህፈት ቤታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ በመግለጽ።

ዘጋቢ አስታወሰኝ በቃሉ – ከማሻ ቅርንጫፍ

ለተጨማሪ መረጃ ከታች ባሉት ድረ ገጾች ይከታተሉን!

Facebook=https://www.facebook.com/profile.php?id=61552831883490

telegram =https://t.me/mashafmsheka

tiktok=https://www.tiktok.com/@masha_fm103.8?_t=8h8vFNn1ToE&_r=1

YouTube=https://youtube.com/@MashaFM-op5hb?si=4gRo1QtHJYQoGZqY2q

Instagram=https://instagram.com/mashafm2023?igshid=MWFsc2NqcTJ2cWJhcg==

Twitter =https://twitter.com/masha_fm98

WhatsApp= https://whatsapp.com/dl/

website:www.mashafm.gov.et

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን።

You may have missed