November 7, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አሁን ላይ በሁሉም አካባቢዎች እየተስፋፋ የመጣዉን የወባ በሽታ ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ተጠየቀ፡፡

በሸካ ዞን የማሻ ከተማ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት በቅድሚያ ለወባ በሽታ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አጎበር የማዳረስ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

የማሻ ከተማ ጤና ጥበቃ ጽህፌት ቤት ኃላፊ አቶ ክቡርሰው ዓለሙ እንደገለፁት ከአሁን በፊት በከተማ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የወባ በሽታ እየተስፋፋ መምጣቱን ገለፀው ስርጭቱን ለመከላከል የኬሚካል ርጭትና አጎበር የማዳረስ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጽህፈት ቤቱ በከተማው በመጀመሪያ ዙር 1ሺህ 25 ተጋላጭ እማና አባወራዎችን በመለየት የአጎበር ሥርጭት እያከናወነ ቢሆንም ይህም አቅርቦት በቂ ባለመሆኑ ሁሉም በዘርፉ በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንድወጣ ጠይቀዋል ::

አሁን ያለውን የአጎበር ስርጭትን በተመለከተ ለነፍሰጡር እናቶች፣ ለሚያጠቡ እናቶች እና ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህፃናት የሚገኙበትን በመለየት በቅድሚያ የማዳረስ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ነው ኃላፍው የገለፁት፡፡

የወባ በሽታ አሁን ባለው ሁኔታ የስርጭቱ መጠን አሳሳቢ መሆኑን በመረዳት ህብረተሰቡ ትኩረት ሰጥቶ የተለያዩ ውሃ የቋጠሩ ቦታዎችን በመለየት በማፋሰስ እና በማዳፈን ሊከላከል እንደሚገባም አክለዋል፡፡

በወቅቱ አጎበር ሲሰጣቸው ካገኘናቸው የማሻ ከተማ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ዘርትሁን ታከለ እና ወይዘሮ ሳልልሽ እምሩ እንደተናገሩት ከአሁን በፊት የአጎበር ተጠቃሚ ካለመሆናቸው የተነሳ ስጋት ፈጥሮባቸው እንደነበር ገልጸው አሁን የወሰዱትን አጎበር በአግባቡ በመጠቀም የስርጭቱን መጠን እንደሚቀንሱ ጠቁመዋል::

የወባን ስርጭትን ለመቀነስ አጎበርን መጠቀም ብቻ በቂ አለመሆኑን ያስረዱት አስተያየት ሰጭዎቹ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አከባቢውን ከማጽዳት ባለፈ አጎበርን በተገቢ እንዲጠቀም ጠይቀዋል።

ዘጋቢ ልጃለም ማሞ- ከማሻ ቅርንጫፍ

ለተጨማሪ መረጃ ከታች ባሉት ድረ ገጾች ይከታተሉን!

Facebook=https://www.facebook.com/profile.php?id=61552831883490

telegram =https://t.me/mashafmsheka

tiktok=https://www.tiktok.com/@masha_fm103.8?_t=8h8vFNn1ToE&_r=1

YouTube=https://youtube.com/@MashaFM-op5hb?si=4gRo1QtHJYQoGZqY2q

Instagram=https://instagram.com/mashafm2023?igshid=MWFsc2NqcTJ2cWJhcg==

Twitter =https://twitter.com/masha_fm98

WhatsApp= https://whatsapp.com/dl/

website:www.mashafm.gov.et

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን።