የፊታችን ታህሳስ 28 የሚከበረዉን የገናን በዓል በማስመልከት ግብይት ሲያደርጉ ያነጋገርናቸው ሸማቾችና ሻጮች እንደገለፁት በበዓሉ ምከንያት አንዳንድ የባልትና ውጤቶች ላይ ጭማሪ እንዳለ ገልፀው ጭማረውም ከዚህ በፊት ከነበረው የአስር እና የአምስት ብር ልዮነት ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል።
በዚህም ሽንኩርት በኪሎ ከ130 እስከ 140 ብር፣ ነጭ ሽንኩርት በኪሎ ከ 240 እስከ 260 ብር ሲሸጥ መዋሉንና በርበሬ ላይም በኪሎ የሀያ ብር ጭማሪ ሲታይ በዚህም በርበሬ በኪሎ 320 ብር ሲሸጥ ውሏል ።
የዶሮ፣ የበግ፣ የፍየል እና የቀንድ ከብቶችም በዛሬው ገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ ሲሸጡ መዋላቸውን ያነሱት ገበያተኞቹ ለአብነትም በሬ ዝቅተኛ ከ35ሺህ እስከ 40ሺህ መካከለኛ 45 ሺህ እስከ 50 ሺህ እንዲሁም ከፍተኛ 55 እስከ 60 ሺህ ሲሸጥ የዋለ ሲሆን ይህም ከባለፈው በዓል ገበያ ጋር ሲነፃፀር ቅናሽ የታየበት መሆኑን ገልጸዋል።
የበግ ገበያም ከ 5,000 ሺህ እስከ 15,000 ሲሸጥ መዋሉንም አንስተው የፍየል ገበያን በተመለከተ ከ4ሺ እስከ 8ሺ ብር ድረስ ሲሸጥ ዉሏልም ብለዋል ።
እንድሁም የዶሮ ገበያን በተመለከተ ከ 700 ብር እስከ 1200 ብር ሲሸጥ እንቁላልም ከ 13 ብር እስከ 15 ብር እንደነበር አንስተዋል ።
በአካባቢው አንደኛ ደረጃ የሚባለው ጤፍ 120 ብር በኪሎ ሲሸጥ ደረጃውን የጠበቀ የፈረስ ጭነት ቆጮም 1000 ብር ሲሸጥ መዋሉንና ቅቤ በኪሎ 600 ብር እንዲሁም ዘይት ባለ 3 ሊትር 500ብር እና ባለ 5 ሊትር 800 ብር እንደሆነ ገልጸው ገበያው ከዚህ በፊት ከነበረው የበዓል ገበያ አንፃር የተሻለ እንደሆነም አንስተዋል።
ዘጋቢ ሀና ግርማ – ከማሻ ቅርንጫፍ
ለተጨማሪ መረጃ ከታች ባሉት ድረ ገጾች ይከታተሉን!
Facebook=https://www.facebook.com/profile.php?id=61552831883490
telegram =https://t.me/mashafmsheka
tiktok=https://www.tiktok.com/@masha_fm103.8?_t=8h8vFNn1ToE&_r=1
YouTube=https://youtube.com/@MashaFM-op5hb?si=4gRo1QtHJYQoGZqY2q
Instagram=https://instagram.com/mashafm2023?igshid=MWFsc2NqcTJ2cWJhcg==
Twitter =https://twitter.com/masha_fm98
WhatsApp= https://whatsapp.com/dl/
website:www.mashafm.gov.et
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ።
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።