July 2, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡመድ ኡጁሉ ለይፋዊ የስራ ጉዳይ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገብተዋል

ጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ኡመድ ኡጁሉ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።

ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ኡመድ ኡጁሉና ልዑካቸው በክልሉ ካፋ ዞን ውሽውሽ ሻይ ተክል ልማት አካባቢ ሲደርሱ ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች ተቀብለዋቸዋል ።

ከርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡመድ ኡጁሉ ጋር ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አብረው ተገኝተዋል ።

ርዕሰ መስተዳድር ኡመድ ኡጁሉና ልዑካቸው በኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የውሽውሽ ሻይ ልማት የስራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በክልሉ የአስተዳደርናፖለቲካ መቀመጫ በሆነችሁ ቦንጋ ከተማ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት እና የጋምቤላ ክልል መንግስት የጋራ የሰላምና ልማት ምስረታ በነገው ዕለት ይደረጋል ሲል የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዘግቧል።

ለተጨማሪ መረጃ ከታች ባሉት ድረ ገጾች ይከታተሉን!

Facebook=https://www.facebook.com/profile.php?id=61552831883490

telegram =https://t.me/MashaFmradio

tiktok=https://www.tiktok.com/@masha_fm103.8?_t=8h8vFNn1ToE&_r=1

YouTube=https://youtube.com/@MashaFM-op5hb?si=4gRo1QtHJYQoGZqY

Instagram=https://instagram.com/mashafm2023?igshid=MWFsc2NqcTJ2cWJhcg==

Twitter =https://twitter.com/masha_fm98

WhatsApp= https://whatsapp.com/dl/

website:www.mashafm.gov.et

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን