July 2, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሠላምና ልማት የማይነጣጠሉ የመንግስትና የማህበረሰብ የጋራ ትብብር ውጤት ናቸው

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልና በጋምቤላ ክልል በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ውይይት በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በዚሁ መድረክ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ሠላምና ልማት የማይነጣጠሉ የመንግስትና የማህበረሰብ የጋራ ትብብር ውጤት ናቸው ሲሉ ተናግረዋል ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ሠላምን በማጽናት የማህበረሰቡን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብሮችን በማሳለጥ የልማት አቅሞቻችንን በተጨባጭ ማሳደግ ይጠበቅብናል ብለዋል።

ሠላምን በማጽናት ልማትን በማፋጠን በምናደርገው ርብርብ ውስጥ አይነተኛ ሚና እንዲጫወት የሁለቱን ክልሎች ህዝብ የእርስ በእርስ ትስስር እንዲጎለብት በማድረግ ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ፋይዳዎችን ማሳደግ ትኩረት ልናደርግበት ይገባል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ።

የውስጥ ጉዳዮቻችንን በጋራ በመፍታት ህገወጥ የማዕድንና ሌሎች የምርት ንግድና ኮንትሮባንድ ፣ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን መከላከል የዘወትር ስራዎቻችን ሊሆኑም ይገባል ብለዋል ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ።

የሁለቱ ክልል ህዝቦች በተመሳሳይ የመልክዓ ምድር አቀማመጥ ፣የአየር ጸባይ እንዲሁም በርካታ የጋራ እሴቶችን በሚጋሩ ማህበረሰቦች እና የጋራ ስነ ልቦና ያሏቸው ኢትዮጵያዊያን ናቸውም ብለዋል።

የህዝቦችን ጠንካራ ትስስር ይበልጥ በማጎልበት በሁለቱ አጎራባች ክልሎች ወሰን አካባቢ የሚከሰቱ የወሰን ጉዳዮችን በጋራ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ በመፍታት ኢኮኖሚያዊ ትስስሮችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል በንግግራቸው ።

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡመድ ኡጁሉ በበኩላቸው በጋራ በምናደርገው ሁሉ አቀፍ ስራዎች የሚያጋጥሙንን ችግሮች በጋራ በመፍታት ሀገራችን የጀመረችሁን የብልጽግና ጉዞ ማስቀጠል ይኖርብናል ብለዋል።

በክልሎች አጎራባች አካባቢዎች የሚነሱ ችግሮችን በጋራና በትብብር በመፍታት የህዝቦችን የመልካም ግንኙነት ስራዎችን ማጠናከርም ይገባል ብለዋል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልና በጋምቤላ ብሔራዊ ክልል መንግስት ዞኖችና ወረዳዋች ዘላቂ ሠላም ለማጽናት የተዘጋጀ ሰነድ በክልሉ ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ በሆኑት በአቶ አንድነት አሸናፊ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

በሁለቱ ክልሎች የጋራ ምክክር መድረክ ርዕሰ መስተዳድሮች፣ የክልሎች አፌ ጉባዔዎች፣ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣የአጎራባች ዞኖች አመራሮች እንዲሁም የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ነው።

ደ.ምእ.መ.ኮ.

ለተጨማሪ መረጃ ከታች ባሉት ድረ ገጾች ይከታተሉን!

Facebook=https://www.facebook.com/profile.php?id=61552831883490

telegram =https://t.me/MashaFmradio

tiktok=https://www.tiktok.com/@masha_fm103.8?_t=8h8vFNn1ToE&_r=1

YouTube=https://youtube.com/@MashaFM-op5hb?si=4gRo1QtHJYQoGZqY

Instagram=https://instagram.com/mashafm2023?igshid=MWFsc2NqcTJ2cWJhcg==

Twitter =https://twitter.com/masha_fm98

WhatsApp= https://whatsapp.com/dl/

website:www.mashafm.gov.et

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን