ነዋሪዎቹ በከተማ ወስጥ በግል ባለሀብት እየተገነባ የሚገኘውን የGM ሆቴል ግንባታ ለማጠናቀቅ በእራሳቸው ተነሳሽነት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ ።
በባለሀብቱ አቶ ገዝሃኝ ወላሻ እየተገነባ የሚገኘውን G+3 የህንፃ ግንባታ GM ሆቴል የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን በግንባታው ላይ በእራሳቸው ተነሳሽነት የተለያዩ ድጋፋችን የከተማ ነዋሪዎች እየሰጡ ይገኛሉ።
ካነጋገሪናቸው የከተማ ነዋሪዎች መካከል አንዳንዶቹ እንደገለፁት ለከተማችን ልማት በቁርጠኝነት በመቆም የተጀመሩ መሰረተ ልማቶችን እናጠናቅቃለን ብለዋል።
የማሻ ከተማ ከ1መቶ 12 አመታት በላይ እድሜ ያላት ብትሆንም እንደ እድሜዋ የተፈለገውን ያህል እድገት ባለማየታችን ቁጭት ውስጥ ገብተናል ያሉት ነዋሪዎች ያለማንም ጥያቄ በእራሳችን ተነሳሽነት በባለሀብቱ የተጀመረውን ሆቴል ግንባታ ለማጠናቀቅ በጉልበታችን እገዛ በማድረግ ላይ እንገኛለን ብለዋል።
በከተማችን ውስጥ ከዚህ በፊት ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች ባለመኖራቸው የቱሪስት ማረፍያ የለንም ያሉት ነዋሪዎች ሆቴሉ ሲጠናቀቅ ይህን ችግር ከመቅረፍ በተጨማሪ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንደሚኖሩትም ጠቁመዋል።
አሁንም ከባለሀብቱ ጎን በመሆን የተጀመረውን ሆቴል ግንባታ ከዳር ለማድረስ በቻሉት ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉም ጠቁመዋል ።
የGM ሆቴል ባለበት የሆኑት አቶ ገዝሃኝ ወላሻ በበኩላቸው የሆቴል ግንባታ ከተጀመረ ከሁለት አመት በላይ ያስቆጠረ መሆኑን ገልፀው ይህም እስከአሁን ከ8 ሚልዮን ብር በላይ ጨርሰዋል ብለዋል።
የህንፃ ግንባታ ግብዓቶች ዋጋ ጭማረ ጋር ተያይዘው በሁለት አመት ውስጥ ለማጠናቀቅ የታቀደው የሆቴል ግንባታ አሁን ላይ ሶስተኛ አመት እያስቆጠረ መሆኑን የገለፁት አቶ ገዝሀኝ ሙሉ በሙሉ የሆቴሉን ግንባታ ለማጠናቀቅ እስከ 13 ሚልዮን ብር እንደሚጨርስም ነው የገለፁት።
GM ሆቴል ስጠናቀቅ የተለያዩ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ የገለፁት አቶ ገዝሃኝ ከሚሰጡት አገልግሎቶች ውስጥ ካፈ፣አልጋ ፣የስብሰባ አዳራሽና ለሎች የመዝናኛ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥም ጠቁመዋል።
የከተማ ነዋሪዎች ስለምወዱኝና የእኔን ጥረት ለማበረታታት ስለሚፈልጉ ላደረጉት ትልቅ ድጋፍ ከልቤ አመሰግናለሁ ያሉት አቶ ገዝሃኝ አሁንም ለህዝቡና ለከተማችን ልማት ከዚህ የበለጠ ስራ ለመስራት የቻልኩትን ሁሉ አደርጋለሁ ብለዋል።
ዘጋቢ ወንድማገኝ ገሪቶ ከማሻ ቅርጫፍ
ለተጨማሪ መረጃ ከታች ባሉት ድረ ገጾች ይከታተሉን!
Facebook=https://www.facebook.com/profile.php?id=61552831883490
telegram =https://t.me/mashafmsheka
tiktok=https://www.tiktok.com/@masha_fm103.8?_t=8h8vFNn1ToE&_r=1
YouTube=https://youtube.com/@MashaFM-op5hb?si=4gRo1QtHJYQoGZqY2q
Instagram=https://instagram.com/mashafm2023?igshid=MWFsc2NqcTJ2cWJhcg==
Twitter =https://twitter.com/masha_fm98
WhatsApp= https://whatsapp.com/dl/
website:www.mashafm.gov.et
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።