January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የካፈቾ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል “የቤነ ሻዴዬ ባሮ”ን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በፓናል ውይይቱ የአከባቢው ተወላጆችና ተጋባዥ እንግዶች እየታደሙ ይገኛሉ።

የካፊቾ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል “የቤነ ሻዴዬ ባሮ” ከዛሬው ዕለት ጀምሮ በፓናል ውይይትና በአደባባይ እንደሚከበርም ተገልጿል።

ባህልን መጠበቅን፣ መንከባከብ እንዲሁም በአግባቡ መጠቀም ላይ ትኩረት ያደረገ ጥናታዊ ጽሁፎች በምሁራኞች እንደሚቀርብም ከወጣው መርሀግብር ለመረዳት ተችሏል።

ዘገባው የክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው