January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሉሲዎቹ ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጪ ሆኑ

የኢትዮጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጪ ሆነ፡፡

የኢትዮጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የአንደኛ ዙር ማጣሪያ ሁለተኛ ጨዋታውን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከብሩንዲ ጋር አድርጓል፡፡

ሉሲዎቹ በመደበኛ የጨዋታ ክፍለጊዜ 1ለ1 ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ በመለያ ምት 5 ለ 3 ተሸንፈዋል፡፡

በዚህም ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጪ ሲሆኑ ቡሩንዲ ወደ ቀጣይ ዙር አልፋለች።